ዜማ
በድንኳኔ እልልታ ሙሉ ነውየዘወትር🔊
በድንኳኔ እልልታ ሙሉ ነው በድንኳኔ ዝማሬ ሙሉ ነው በማንነቴ ላይ እግዚአብሔር ታላቅ ነው አዝ ፍላፃውን የጠላቴን ቁጣ መከተልኝ ወደ እኔ እየመጣ በራራልኝ በእርሱ በወዳጄ ሰላም ሰፍኗል በጓዳ በደጄ አዝ የመንገዴን ጥርጊያውን አቅንቶ የሰለለ ጉልበቴን አፅንቶ ከፊት ለፊት በድል ቀድሞልኛል በምስጋናው ከኋላ ስቦኛል አዝ ስላልተወኝ አንዳች አጣህ ብሎ ሙሉ ሰው ነኝ የለኝም ጎዶሎ በከፍታ ብኖር በዝቅታ ደስተኛ ነኝ ሁልጊዜ በጌታ አዝ ማማረርን ማጉረምረም ትቻለሁ አንደበቴን ቅኔ ሞልቻለሁ ቢፈራረቅ ብርሃን ጨለማ ከቶ አልወርድም ከምስጋና ማማ (2)
አምላክ ፈቃዱ ሆኖየመላእክት🔊
አምላክ ፈቃዱ ሆኖ ባያድነንም እንኳ ላንተ አንሰግድም አሉ አናንያ አዛርያ ሚሳኤል(2) ካልበላችሁ ጮማ ካልጠጣችሁ ወተት ብለው ሲያስፈራሩ ይቀድማችኋል ሞት እኛ ግን ተማምነን በፈጣሪያችን መልካችን አማረ ጥሬ ቆርጥመን በበረታች ክንዱ ልጆቹን ታደገ የሚያቃጥል እሳት ውሃ እያደረገ ማን ያድናቸዋል ጠላታችን ሲል መጣልን ተልኮ ቅዱስ ገብርኤል ምንን ተሰምቶት ይሆን ናቡከደነፆር የወጠረው ሴራ ከሽፎ መና ሲቀር ከቶ ምን ሊያመጣ ምንስ ቢሰማው የእግዚአብሔርን አሳብ ንጉሥ አይቀይረው ዛሬ በፈተና በጭንቅ ውሰጥ ያላችሁ በመከራ ጽኑዕ ከኛ ተምራችሁ አይዘገይም እና ኋያል ፈጣርያችሁ ይህ ክፉ ቀን አልፎ ታወሩታላችሁ። 25|ዐ1/2016 አሑድ
እሰይ እልል በሉየመስቀል🔊
እሰይ እልል በሉ እሰይ እልል በሉ ተገኘ መስቀሉ (2) እሰይ እልል በሉ ተገኘ መስቀሉ (2) አዝ የጥል ግድግዳ አበባ የፈረሰበት አበባ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አበባ የታረቀበት አበባ የእግዚአብሔር ልጅ አበባ የነገሰበት አበባ የሞት አበጋዝ አበባ የወደቀበት አበባ አዝ አይሁድ በቅናት አበባ መስቀሉን ቀብረው አበባ ቢከድኑት እንኳን አበባ በቆሻሻቸው አበባ ጌታን መቃወም አበባ ስለማይችሉ አበባ ይኸው ተገኘ አበባ ወጣ መስቀሉ አበባ አዝ ደጉ ኪራኮስ አበባ ሽማግሌው አበባ እሌኒን መራ አበባ በደመራው አበባ ጌታ በእርሱ ላይ አበባ በመሰቀሉ አበባ ጭሱ ሰገደ አበባ ወደ መስቀሉ አበባ አዝ የእምነት ምልክት አበባ መስቀል ነውና አበባ ተራራው ሜዳ አበባ ሆነ እንደገና አበባ እንደተነሳ አበባ ጌታ እንደቃሉ አበባ ከጉድጓድ ወጣ አበባ ዕፀ መስቀሉ አበባ አዝ እኛም በመስቀል አበባ እንመካለን አበባ በእግዚአብሔር ጥበብ አበባ መቼ እናፍራለን አበባ ሞኝነት እንኳን አበባ ቢሆን ለዓለም አበባ ኃይል ጸወን ነው አበባ ለዘለዓለም አበባ አዝ ግድግዳው ፈርሷል አበባ የልዩነቱ አበባ ምድርና ሰማይ አበባ ሆኑ እንደ ጥንቱ አበባ ነፍስና ስጋ አበባ በእርሱ ታርቀዋል አበባ ሕዝብና አሕዛብ አበባ ወንድም ሆነዋል አበባ ዘማሪ ዲ/ን አበበ ታዬ